የአረጋዊያን ቀን ተከበረ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) የአረጋዊያን ቀን በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ ተከበረ።

በዝግጅቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

የዘንድሮው የአረጋዊያን ቀን “የአረጋዊያን የኢትዮጵያዊነት አሻራ ለትውልድ አደራ” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በርካታ የሆኑ አረጋዊያን እና ተጋባዥ እንግዶች በመገኘት ለበዓሉ የተዘጋጀውን ኤግዝብሽን በጋራ ጎብኝተዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ወቅትም ብሔራዊ የአረጋዊያን መርጃ ማእከል የግንባታ ዲዛይን በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና በሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ ይፋ ተደርጓል።

የዛሬ ወጣት የነገ አረጋዊ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ያሉት ፕሬዝዳንቷ አረጋዊያን ትክክለኛ ቦታ የተሰጠው አይደለም እና ሁላችንም በጋራ ልንንከባከባቸው እና ልንጠብቃየው ይገባል ብለዋል።

በግዛቸው ይገረሙ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW