የአረፋ በዓል በጅግጅጋ ከተማ ተከበረ

ሐምሌ 13/2013 (ዋልታ) – 1 ሺህ 442 ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በአል በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ስቴድየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ሙስጠፌ ሙሃመድ ለመላው ዓለም የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርም  በመረዳዳት እንዲሁም የተቸገሩና የታመሙ ሰዎችን በመጎብኘት መሆን እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡

የጅግጅጋ ከተማ  ነዋሪ ህዝበ ሙስሊም ምዕመናን በበኩላቸው  በዓሉ ሰላም የሰፈነበትና እንደነበር በመግለጽ÷በዓሉ ትላንት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ማግስት መከበሩ ደስታቸውን እጥፍ  ድርብ እንዳደረገው መናገራቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዓሉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ሙስጠፌ ሙሃመድ፣ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሐላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ከህዝበ ሙስሊም ጋር በመሆን አክብረዋል፡፡