የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ

የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ሥነ ስርዓት

ጥር 12/2014 (ዋልታ) የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በአዳማ ከተማ ተፈጽሟል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና ለኦሮሞ ኪነ ጥበብና ለአፋን ኦሮሞ እድገት ካደረገው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የኦሮሞ ሕዝብ እና የብሔር ብሔረሰቦች መብት እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ታላቅ አርቲስት ነበር፡፡

አርቲስቱ በተለይ “Tokkummaa”, “Isin yaamti harmeen” በሚሉ እና የሕዝብን አንድነት በሚያጠናክሩ የሙዚቃ ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡

በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የአርቲስቱ ወዳጆች ተገኝተዋል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና በድሬዳዋ ከተማ ቀፊራ ገንደ ጋራ ነበር በ1940 ዓ.ም የተወለደው፡፡