የአርቲስት አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነሥርዓት

የአርቲስት አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነሥርዓት

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) የአርቲስት አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነሥርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከናውኗል።

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ  የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ጉልህ አበርክቶ የነበረው ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነሥርዓት ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም የሙያ አጋሮቻቸው እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ በበርካታ የአለም ሀገራት ያስተዋወቀው አንጋፋው አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ለሀገሩ ባበረከተው አስተዋፅኦ ሊመሰገን እንደሚገባ በቀብር ስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሙያ አጋሮቹ ገልፀዋል።

በቁምነገር አህመድ