የአብዬን ሰላም የማጠናከር ተልዕኳችንን በአስተማማኝ ወታደራዊ ዝግጁነት በውጤት እያስቀጠልን ነው – ሌ/ኮሎኔል ክፍሎም ገ/ማርያም

ጥር 16/2014 (ዋልታ) “የአብዬን ሰላም የማጠናከር ተልዕኳችንን በአስተማማኝ ወታደራዊ ዝግጁነት በውጤት እያስቀጠልን ነው” ሲሉ በአብዬ የዘጠነኛ ሁለገብ ሎጀስቲክስ ዋና አዛዥና የናሽናል ቲም አስተባባሪ ሌ/ኮሎኔል ክፍሎም ገ/ማርያም አስታወቁ።
የሁለገብ ሎጀስቲክስ ሻምበሉ ሁለንተናዊ ዝግጁነት ከዓለም ዐቀፍ የሰላም ማስከበር መመዘኛ አንፃር ጥራትና ብቃቱ በመስኩ ሙያተኞች ተፈትሾ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ስለመገኘቱም አረጋግጠዋል።
በግዳጅ ቀጣናችን የሚገኘው ማኅበረሰብ ሰላሙ ተጠብቆለት መኖር እንዲችል አድርገናል ያሉት ከፍተኛ መኮንኑ የተሰጠንን ተልዕኮ በድል እየተወጣን በመገኘታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
የሁለገብ ሎጀስቲክስ ሻምበል በአብዬ ዓለም ዐቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በአስተማማኝ ዝግጁነት አመርቂ ተግባር ሲወጣ የቆየ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።