የአንድነትና የአሸናፊነት ድል በማጠናከር ለዘላቂ ልማትና ሰላም መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ

 

ጥር 19/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ሙሐመድ በኢትዮጵያ አሁን የታየውን አንድነትና የአሸናፊነት ድል በማጠናከር ለዘላቂ ልማትና ሰላም መትጋት እንደሚገባ ገለጹ።

በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች በጋምቤላ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጋምቤላ ከተማ ገብተዋል።

ዳያስፖራዎቹ በጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ሙሐመድ ለተደረገተላቸው አቀባበል አመስግነው ጋምቤላ ሲገቡ ያዩት ሰላምና የሕዝቦች አንድነት እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸው ጉዳይ አሳስቧቸው በአካል በመገኘት እያደረጉ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

ዳያስፓራዎች በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የመስህብ ሥፍራዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ጉብኝትና ውይይት እንደሚያደርጉ የኤዜአ ዘገባ አመላክቷል፡፡