የአንድ ዓመት ደመወዙን ለመከላከያ ሰራዊት የለገሰው ዶክተር

ዶክትር ኤልያስ ጉልማ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) ዓለም ላይ ካሉ የሙያ ዘርፎች ሁሉ ግንባር ቀደሙንና በዋጋ ደረጃ ውድ የሆነውን የህክምና ሙያ እንዳስተማረችው ሁሌም በውስጡ የሚመላላስበት እውነት ሆኖ አገኘው፡፡

እናም ይህን ሃገራዊ ውለታ መመልስ እንደማይችል ቢያምንም የውስጡን ሃሳብ ይጋራው ዘንድ ቃል ለገባለት ሙያ ዘወትር ታምኖ ያገለግላል፡፡

በሚሰራበት የአዋሳ ከተማ አዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክትር ኤልያስ ጉልማ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና የልብ ምርመራና ህክምና ባለሙያ ሆኖ ከማገልገሉ ባለፈ በደቡብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል በተደራቢነት ያገለግላል፡፡

ሃገርን በማትተካው እናት የሚመስላት ዶክተር ኤሊያስ እናት ስትቸገር ማየት ህመሙ ከባድ እንደሆነ በመግለጽ፣ ሃገሬ የሆነችልኝ ከቃልም ከአድራጎትም በላይ በመሆኑ ሁለንተናዬን አሳልፌ ለመሰጠት ዝጉጁ ነኝ ብሏል፡፡

በዱር በገደል ውድ ህይወቱን እየሰዋ ሃገር ለሚያቆመው የመከላከያ ሃይል መላው ህዝባችን ተከፍሎ የማያልቅ ብድር አለበትም ብሎ ያምናል ዶ/ር ኤልያስ፡፡

በተለይም በአሁኑ ሰዓት እናት ሃገር ኢትዮጵያ የገጠሟትን ችግሮች ለመፍታት አድረን ለመገኘት የምንሳሳላትን ነፍስ እየሰጠ ትውልድ የሚያስቀጥለውን የመከላከያ ሃይል መርዳትና በምንችለው ሁሉ አብሮነታችንን መግለፅ የታሪክ ባለቤት ያደርገናል ብሏል፡፡

ሃገርን በሙያው እያገለገለ የሚገኘው ዶክተር ኤሊያስ ጉልማ ቤቴን ትዳሬን ሳይል የአንድ አመት ደመወዙን ለመከላከያ መስጠቱ ደስታን ወልዶለታል፡፡

ዶክተሩ የወር ደመወዙ 13114 ሲሆን፣ ለመከላከያ ድጋፍ ይሁንልኝ ብሎ የለገሰው የአንድ አመት ደመወዙ 157368 (አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ስድሳ ስምንት) ብር ይሆናል፡፡

ሃገርን ለማዳንና ለኢትዮጵያችን ክብር ለሚሰዋ ሃይል ያለውን መደገፍ ከሚሰጠን መንፈሳዊ እርካታ በተጨማሪ ሃገራዊ ግዴታችንም ጭምር በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የጀመረውን ሃገራዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ዶክተር ኤልያስ አስምሮ የተናገረ እውነት ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡