ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) “ኑ ጠቃሚ እሴቶቻችንን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ የአውራምባ ማኅበረሰብ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሠ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር ከአውራምባ ማኅበረሰብ የሥራ ባህል በመቅሰም ኢትዮጵያ ለጀመረችው የልማት እና እድገት ጎዳና መዳረሻነት መጠቀም ያሻል ሲሉ ተናግረዋል::
የአውራምባ ማኅበረሰብ የ50 ዓመታት ጉዞ በርካታ ውጣ ውረዶችን በማለፍ ዓለምን ሊቀይር የሚችል እሳቤን በማንገብ ከፆታ እኩልነት እስከ ጠንካራ የሥራ ባህል መተጋገዝንና መተባበርን በተግባር ያሳያ የማኅበረሰብ ክፍል በመሆኑ ከማኅበረሰቡ መልካም እሴቶችን በመቅሰም ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል ተብሏል፡፡
የአውራምባ ማኅበረሰብ መስራች ዙምራ ኑሩ (ዶ/ር) ማኅበረሰቡ በርካታ መልካም እሴቶችን የያዘ በመሆኑ መልካም እና ገንቢ የሆኑ እሴቶችን ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍል ማስፋፋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ሔብሮን ዋልታው (ከአውራምባ)