የአውሮፓ ኅብረት መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን በአዎንታ እንደሚቀበል ገለጸ

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን በአዎንታ መቀበሉን ገለጸ።

ኅብረቱ በትዊተር ገጹ በወጣው መልዕክት ሰብኣዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ በአፋጣኝ ለማድረስ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።

መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብኣዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ትናንት ማሳወቁ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!