የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ፡፡

የምክር ቤቱ ጉባኤ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግር በይፋ አስጀምረዋል።

ምክር ቤቱ በሁለት ቀን ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የከተማ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚገመግም ሲሆን የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ማጽደቅ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል፡፡