የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሀ ግብር አካሄደ

ነሃሴ 08/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሰራተኞች እና አመራሮች በኮየ ፈጬ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡
በኮየ ፈጬ የጋራ መኖርያ ቤቶች በተከሄደው የአረንጓዴ አሻራ በመርሀ ግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳድር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጥላሁን ከበደ የተተከሉት ችግኞች ለአካባቢው ውበትና የአየር ንብረት መዛባት እንዳያስከትል ስለሚረዱ ከመትከል ባሻገር ተገቢ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ቤት ከመስራት ጎን ለጎን አካባቢን የማስዋብ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት አክለው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ለአካባቢው አርሶአደሮች ከ 1ሺህ በላይ የማንጎ፣ ዘይቱን፣ አቮካዶ እና የጌሾ ችግኞችን በስጦታ አበርክቷል፡፡
(በአመለወርቅ መኳንንት)