የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት ይሰጣል

የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ጃንሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ የከተማ አስተዳደር ባዘጋጀው የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወር በተወሰነው መሰረት የዕጣ ማውጣት ስርዓቱ ተጠናቆ ውል መዋዋል ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ውሉ  ዛሬ  ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ ጃንሜዳ የነበረው አትክልት ተራ በአዲስ አበባ ላፍቶ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በተገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ተዘዋውሮ ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡