የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

 

ሐምሌ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በምክር ቤቱ 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሿሚዎችን የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚህም
1. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ – የአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አንድነት ብዙሰው ታመነ- ምክትል ዋና ኦዲተር
3. አቶ ቁሴ ለታ ዋቅጅራ- ምክትል ዋና ኦዲተር
4. አቶ ያብባል አዲስ ጎበዜ – የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ
5. አቶ ማሾ ኦላና- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው እንዲያገልግሉ መሾማቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡