የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጤና መድህን 144 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን 144 ሚሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የማህበረሰብ የጤና መድህን መዋጮ ከነበረበት 350 ብር ወደ 500 ብር ከፍ ማለቱም ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የጤና መድህን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን 144 ሚሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት የመክፈል አቅም ለሌላቸው 231 ሺሕ ነዋሪዎች 29 ሚሊዮን ብር ወጭ በመሸፈን የነፃ ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የመንግስት ሰራተኛውን ጨምሮ ፍላጎት ያለውን የማህበረሰብ ክፍል የጤና መድህን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት ለመዘርጋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!