የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ምክር ቤት ምስረታ መጀመር

የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ምክር ቤት ምስረታ

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምስረታ ስነ-ሥርአት በከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት መካሄድ ጀምሯል።

እንደ ከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት መረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ተመራጭ የምክር ቤት አባላትም ወደ አዳራሽ እየገቡ ነው።

በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝብ ድምፅ የተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ አዲስ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ይመሰረታል።