የአዲስ ዋልታ እጅግ በርካታ ፈጣን ለውጦች አስገርሞኛል – ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት

ሰኔ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በጣም ብዙና ፈጣን ለውጥ ማሳየቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ተናገሩ።

አማካሪው ዛሬ ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬትን የጎበኙ ሲሆን ከኮርፖሬቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ ሐሰን ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪው አዲስ ዋልታ አዳዲስ ፕሮግራሞች መጀመሩን፣ በአዳዲስ ሀሳቦችና በአዲስ አቀራረብ መምጣቱን እንዲሁም የቢሮና የሥራ ቦታን ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ አስገራሚ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል።

በተለይ በሬዲዮ ዘርፍ ላይ ያዩት ለውጥ እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል።

በዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት የተደረገው ለውጥ እንዳስገረማቸው የጠቀሱት ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ሚዲያው ለአገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

መንግስት ለዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት የተለያዩ ጉዳዮችን እያሰበ ነው ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ተግባራዊ ሲደረጉ ደግሞ የበለጠ እየዘመነና እያደገ እንደሚሄድ ተናግረዋል።

የለውጥ ማኅበረሰብ፣ የሚዲያዎች ለውጥ፣ እድገትና ጉድለቶች እንዲሁም ተቋማትን የተመለከቱ ጉዳዮች በውይይቱ ላይ ተነስተዋል።