የአዳዲስ ክልሎች መዋቀር መንግሥት ለትክክለኛ ፌደራሊዝም እውን መሆን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ተባለ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ዛሬ የተመሰረተውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ምስረታ በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የአዳዲስ ክልሎች መዋቀር መንግሥት ለትክክለኛ ፌደራሊዝም እውን መሆን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕዝቦች የዘመናት የአስተዳደር ጥያቄ በለውጡ መንግሥት ምላሽ በማግኘቱም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ለአዲሱ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ለተሾሙት ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መመኘታቸውንም ከሐረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክቷል፡