የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን መፍታት ላይ ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን መፍታትና የአኅጉሯን ሁለንተናዊ ስብዕናን ማጠናክር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ውይይቱ አዳማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ውይይቱ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያጠናክር ሲሆን ሀገሪቱ የአፍሪካ የነጻነት ቀንዲል መሆኗም ተጠቅሷል፡፡

በመድረኩ የአፍሪካ ኅብረት ተወካይ እና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡

ሜሮን መስፍን (ከአዳማ)