የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

                                                የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና

ግንቦት 27/2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ልማትና ትራንስፎርሜሽን መደነቃቸውን እና ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በመገናኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ያደረገው የ1.7 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አክንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልም ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርከች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።