የአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ

ግንቦት 19/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ እየተካሄደ ነው።

በትናትናው ዕለት ኢኳቶሪያል ጊኒ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት በጀመረው የአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የሕብረቱ ጉባኤ በአኅጉሪቱ የተጋረጠውን ወቅታዊ የሰብአዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የአፍሪካ መሪዎች ባደረጉት ጥረት ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም ከሰብአዊ ተግዳሮቶች ጋር ተያይዞ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ፣ ከግጭት በኋላ ማገገምን በተመለከተ እንዲሁም ሰላም እና ልማትን ከማሳደግ አንጻር ዘላቂ መፍትሄዎችን በመለየት ዙሪያ ውይይት አንደሚያደርግ ተገልጿል።
ከዚህ ባሻገር መሪዎቹ በአኅጉሪቱ ስላለው ሽብርተኝነት እና ኢ-ሕገመንግስታዊ የመንግሥት ለውጥ ዙሪያም እንደሚወያዩ የኢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW