የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን ገለጸ

ሰኔ 16/2013(ዋልታ) – በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሥርዓቱን በጠበቀ፣ በሠላምና ታዓማኒነት መጠናቀቁን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ገለጸ።

ቡድኑ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ የምርጫውን የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ተዘዋውሮ መታዘቡን ገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ምርጫው ሰላማዊና ቅደም ተከተላዊ ሥርዓቱን ተከትሎ መከናወኑን ነው የኅብረቱ የምርጫ የታዛቢ ቡድኑ ዛሬ በሰጠው የመጀመሪያ መግለጫ ያሳውቋው።

የታዛቢ ቡድኑ መሪ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆ ምርጫው ሥርዓቱን በጠበቀ፣ በሠላምና ታዓማኒነት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ታዛቢ ቡድኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2007 የኅብረቱ የዴሞክራሲ፣ ምርጫና አስተዳደር ቻርተር መሰረት ተከትሎ ነው ምርጫውን የታዘበው።

ቡድኑ በአፍሪካ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አስተዳደር በተመለከተ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2002 ያወጣውን የመርህ ድንጋጌም መሰረት አድርጓል ብሏል።