የአፍሪካ ወጣቶች ለአፍሪካ ችግሮች መፍትሄ እንዲሆኑ እየሰተራ መሆኑ ተገለፀ

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ወጣቶች ለአፍሪካ ችግሮች መፍትሄ እንዲሆኑ አፋሪካውያን በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ።

‘ጄት ኤጅ’ ከኢፌዲሪ ስራ ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን አፍሪካውያን ወጣቶች ለአፋሪካ ችግሮች መፍትሄ እንዲሆኑ የሚያስችል መድረክ አዘጋጅቷል።

የስራ አቅም ያላቸውን ወጣቶች በመመልመል እና በማሰልጠን ለአገራቸው እና ለአፋሪካ ጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራው ‘ጀት ኤጅ ኔሽን ቢዩልዲንግ’ የተባለው ተቋም ሁለተኛ ዙር የውይይት፣ ኤግዚብሽን እና የእውቅና ዝግጅቱን በአዲስ አበባ አድርጓል።

በዚህ አህጉራዊ ዝግጅት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአለም ከሚገኙት ወጣቶች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው በአፋሪካ ይገኛል ያሉ ሲሆን፣ ይህንን ሀይል ስራ በመፍጠር መስራት እንዲችል ማድረግ ከፋተኛ ለውጥ በአህጉሪቷ ላይ እንዲመዘገብ ያደርጋል ብለዋል።

የአፉሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፋሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱል ከማል በበኩላቸው ለአፋሪቃ ልማት እና ከድህነት መውጣት የወጣቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአፋሪካ ልማት ባንክ የስራ እድልን ለመፍጠር እየሰራ ነው ብለዋል።

የ2011 ‘ጄት ኤጅ’ የወጣቶች ስራ ፈጠራ በኢትዮጵያ ሲካሄድ ከበርካታ የአፋሪካ አገራት የተወጣጡ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

(በቁምነገር አህመድ)