የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል 220 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት አገኘ

ሐምሌ 30/2013(ዋልታ) – የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ለአፍሪካ ሃገራት የሚሆን 220 ሚሊዮን የኮቪድ -19 ክትባት ማግኘቱ ተገለፀ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ከኤስፒኤን ጋር በተደረገው ስምምነት እ.አ.አ መስከረም 2022 ላይ 220 ሚሊዮን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ወደተለያዩ አፍሪካ አገራት እንደሚሰራጭ ተነግሯል፡፡

በነሐሴ ወር የመጀመሪያው 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶዝ መድሃኒት ወደ 35 አገሮች ይላካሉ መባሉን ኢዜአ ኤስ ኤ ቢ ሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ይህ ክትባት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ስትራይቭ ማሲዪዋ የሚመራ ሲሆን በአፍሬክስም ባንክ የተገኘ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ብድር ድጋፍ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ አባል ሀገራት የኮቪድ -19 የማያቋርጥ የክትባት ስርጭት ለማካሄድ ስምምነት አጠናቃለች ተብሏል።

የአፍሪካ ህብረት በኮቪድ-19 ልዩ መልዕክተኛ ስትራይቭ ማሲዪዋ ስለስምምነት ሲናገሩ ከደቡብ አፍሪካ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቱ በዩኒሴፍ በኩል ወደ ተለያዩ አገራት እንደሚያጓጉዝ መረጃው አስታውሷል።