የአፍሪካ ጊዜ አሁን ነው፣ አብረን ከድህነት ጉድጓድ በፍጥነት መውጣት እንችላለን – ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የአፍሪካ ጊዜ አሁን በመሆኑ ልንተባበር ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቲውተር መልዕክታቸው አብረን ከድህነት ጉድጓድ ፣ አለመተማመን እና ክብርን ከመለመን በፍጥነት መውጣት እንችላለን ነው ያሉት።
በምጣኔ ሃብት ውኅደት፣ ሃብታችንን እና እውቀታችንን በማጣመር አጀንዳ 2063 ማሳካት እንችላለንም ብለዋል።