ነሐሴ 17/2014 (ዋልታ) የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እንዲሁም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጄኔራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደህንነት እና ወታደራዊ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሂደዋል።
ለልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
ልዑኩ በነበረው ቆይታ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ኢንስቲትዩቱ እያካሄደ ስለሚገኘው ዘርፈ ብዙ ክንውኖች በዋና ዳይሬክተሩ አማካኝነት ገለጻ ተደርጎለታል።