ሐምሌ 20/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንደስትሪያል ፓርክ 3000 ለምግብነት የሚውሉ ችግኝ ተክለዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት አገራችን ባለፉት 6 አመታት ከ25 ቢሊየን በላይ ችግኞች በመትከል በዓለም የራሷ አሻራ ማስቀመጧን አውስተው የዘንድሮ ችግኝ ተከላ ኘሮግራምም በሀገር አቀፍ ደረጃ “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የተከላ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።
አረንጓዴ አሻራ አየር ንብረት ሚዛን ከመጠበቅ በተጨማሪ አገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው እንቅስቃሴ የራሱ አወንታዊ ሚና ይጫወታል ማለታቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሠራተኞች የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 2 ሚሊየን ብር እና የቁሳቁስ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡