የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ

 

የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አምብሮሲ ድላሚኒ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራት ሳምንታት በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ገልጸው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኙ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ለሞታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሮረናቫይረስ ከተያዙ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር ተብሏል።

ሆኖም የ52 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ሆስፒታል ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ትናንት ከሰዓት ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡት በፈረንጆቹ 2018 ጥቅምት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአሁኗ ኢስዋቲኒ የቀድሞዋ ስዋዚላንድ ንጉስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡