የኢትዮጵያና ቱርክን የፍትሕ ዘርፍ ግንኙነት ለማጠናከርና የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ

ነሐሴ 17/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያና ቱርክን የፍትሕ ዘርፍ ግንኙነት ለማጠናከር እና በትብበር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ።

በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው የተመራ የልዑካን ቡድን በቱርኪዬ የስራ ጉብኝት አድርጓል።

ልዑኩ ከቱርኪዬ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ያኩፕ ሞኡል ጋር በሁለቱ አገራት የፍትህ አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በትብበር ለመስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል ተብሏል።

ከውይይቱ በኋላም በኢትዮጵያ እና በቱርኪዬ መካከል በትብብር ለመስራትና የባለሙያዎችን እንዲሁም የተቋማቱን አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ትብብሮችን ለማስጀመር በፍትህ እና ፎረንሲክ ዘርፎች ሁለት የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል።

የልዑካን ቡድኑ በቱርኪዬ የኢፌዴሪ አምባሳደር አደም መሀመድ ጋር የተወያየ ሲሆን ከቱርክ መንግስት ጋር በቀጣይ ሊደረጉ በሚገባቸው የሕግና ተያያዥ ጉዳዮች ትብብር ዙሪያ ምክክር አድርጓል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡