መስከረም 5/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያና ኬኒያ መንግስታት የሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከል የአሰራር መመሪያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የሚካሄደውን የንግድ ትብብር ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን የስችላል ተብሏል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ በኩል የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ሲሆኑ፣ በኬኒያ በኩል የድንበር አስተዳደር ሴክሬታሪያት ዋና ጸኃፊ ኬኔዲ ኒያ ዮ መሆናቸው ተገልጿል።
የሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በኬንያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ተመርቆ ሥራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።