የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት ገቢ ወደ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በስትራቴጂክ እቅድ መያዙ ተገለጸ

ሐምሌ 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት ገቢ በ15 ዓመታት ውስጥ ወደ 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በስትራቴጂክ እቅድ መያዙ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል በጄኔቫ ስዊዘርላንድ በተዘጋጀው የቡና ቅምሻ ፕሮግራም ላይ የተሳተፈች ሲሆን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በመርኃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ ቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች እና እንቅፋቶች፣ ብሎም የቡናን ዘርፍ ለማሳደግ የመንግሥት አጠቃላይ ስትራቴጂ ምን እንደሚመስል ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በቅርቡ በወጣው ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ መንግሥት ችግሮቹን ለመፍታትና የኢትዮጵያን የቡና ምርት ገቢ በ15 ዓመታት ውስጥ ወደ 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ አንስተዋል፡፡

የአርሶ አደሩን ገቢ ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና የሥራ እድል ለመፍጠር ስትራቴጂ መነደፉን ጠቁመው በ2033 በዓለም ገበያ የምታቀርበው የዓለም ገበያ ድርሻ በ2033 ወደ 1 ነጥብ 26 ሚሊዮን ማድረስ መታቀዱን አንስተዋል።