የኢትዮጵያን ደረጃ ያላሟሉ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን ደረጃ ያላሟሉ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻና የኢንስፔክሽን ስራ ከደረጃው በታች የሆኑ ገቢ ምርቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪና የገቢ እቃዎች የጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን ገቢ ምርቶች ላይ የኢንስፔክሸን ሥራ ለማከናወን አቅዶ በ586 ሺህ 746 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የገቢ ዕቃዎች ላይ የኢንስፔክሽን ሥራ ተከናውኗል።

እርምጃ የተወሰደባቸው ገቢ ምርቶችም፤

  • 3.5 ሜ.ቶ LED አምፑል
  • 25.8 ሜ.ቶ የኤልክሪክ ማከፋፈያ
  • 3ሺህ 688 ካርቶን መጠን ያለው የሀይል አባካኝ አምፖል፣
  • 9 ካርቶን የታሸገ ወተት
  • 55.3 ሜ.ቶ የአተር ክክ
  • 10.4ሜ.ቶ ሩዝና 693.8 ቶን ቀይ ሽንኩርት መሆናቸው ተገልጸዋል።