የኢትዮጵያዊነት ቀንን በተመለከተ የፓናል ውይይት

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) “ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ” በሚል የኢትዮጵያዊነት ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በፓናል ውይይቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡