የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስራ አስፈፃሚዎች እና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አከናወኑ

ሐምሌ 30/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስራ አስፈፃሚዎች እና ሰራተኞች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መለስ ዜናዊ መታስቢያ ፓርክ ”አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን አከናውነዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዩሀንስ አያሌው (ዶ/ር) አስጀምረዋል።

ባንኩ እንደ ሀገር በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሲሳተፍ ለ4ኛ ጊዜ ቢሆንም ችግኝ መትከል ከጀመረ 8 ዓመታትን ማስቆጠሩን ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት።

ባንኩ ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር መሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ወደፊትም ይህን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባንኩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

በተለያዩ የሀገር ልማት ስራዎች እየተሳተፈ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ማህበራዊ ስራዎች ላይ እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸዋል።

ባንኩ በ4 ዙር ባከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ12ሺሕ በላይ ችግኞችን መትከሉ የተገለፀ ሲሆን በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 2 ሺሕ 155 ችግኞች መተከላችው ተመልክቷል።

በፌናን ንጉሴ