የኢትዮጵያ መንግስት በኢስታንቡል በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

ኅዳር 5/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መንግሥት በትናንትናው ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ኢስቲካል ጎዳና በተፈጸመው የሽብር ድርጊት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡

መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጣው መግለጫ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን በመመኘት በተፈጸመው የሽብር ጥቃት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውም እንዲያገግሙ ተመኝቷል፡፡

በደረሰው አደጋ የኢፌዴሪ መንግሥት ከቱርክ መንግስት እና ሕዝበ ጎን መቆሙንም አስታውቋል፡፡

በቱርክ ኢንስታንቡል በተፈጸመ “የሽብር” ጥቃት 6 ሰዎች መገደላቸውን እና 81 ሰዎቸ መቁሰላቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ትናንት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት 10 ሰዓት አካባቢ ያጋጠመው ፍንዳታ በሴት የተፈጸመ የሽብር ጥቃት ነው ሲሉም የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉአት ኦክታይ መናገራቸውን ዘገባው አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW