ጥር 10/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ማስዳር ኩባንያ የ500 ሜጋ ዋት ሁለት የሶላር ጣቢያ/የፀሐይ ብርሃን ኢነርጂ በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስምምነቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ኢትዮጵያ ሰፊ የታዳሽ ኃይል ሀብት እንዳላት ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርቦን ልቀት ዜሮ የማድረግ ኢላማ ታዳሽ ሀብታችንን ለመጠቀም እና አስተማማኝ፣ ንፁህ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኃይል ለኢትዮጵያ እና ለሌሎችም ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ዐቅም እና እድል ነው ሲሉም አክለዋል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ትናንት ማምሻውን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት አስታውቋል።