የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 4 አዳዲስ ምርቶችን ለግብይት ማቅረቡን አስታወቀ

የካቲት 17/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 4 አዳዲስ የቅመማቅመም እና የጓያ ምርቶችን ለግብይት ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ያለፋትን 13 ዓመታት የምርት ጥራትን በማስጠበቅ የተሳለጠ የግብይት መድረክ ሆኖ የቆየው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የጥቁር አዝሙድ፣ ድምብላል፣ አብሽና ቁንዶ በርበሬ ቅመማቅመሞችን እንዲሁም የጓያ ምርትን ግብይት መጀመሩን ነው የገለጸው፡፡

የቅመማቅመሞቹ ወደ ግብይት ስርዓቱ መቀላቀል በተለይም በወጭ ንግድ ላይ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል፡፡

በሳሙዔል ሓጎስ