ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በቻን ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ዛሬ ይጫወታል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያ 0 ለ 0 መለያየታቸው ይታወሳል።
የዋሊያዎቹ ዋና አሰጣኝ ውበቱ አባተ ለጨዋታው ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ በታንዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲዬም ነው የሚደረገው፡፡