የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሆነ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ፡፡

ቡድኑ በ17ኛው ሳምንት የሊጉ ውድድር አዳማ ከተማን 2ለ1 መርታቱን ተከትሎ ነው አሸናፊነቱን ያረጋገጠው፡፡ በውድድር ዘመኑ ቡድኑ 43 ነጥቦች መሰብሰቡም ታውቋል፡፡

በተጨማሪም የቡድኑ ተጫዋቾች ረሂማ ዘርጋው በ16 እና ሎዛ አበራ በ15 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ደረጃ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ መጋቢት 19 ቀን በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡