የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከቀናት በኋላ ወደ በረራ ሊያስገባ ነው

                                                    የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ጥር 16/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀናት በኋላ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ወደ በረራ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን ለድጋሚ በረራ ዝግጁ ያደረገው ከሚመለከታቸው ዓለም ዐቀፍ የበረራ ተቆጣጣሪዎችና ሌሎች በርካታ የቁጥጥር አካላት የተደረገውን ተደጋጋሚ የደኅንነት ማረጋገጫ ተከትሎ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለበረራ ዝግጁ ያደረገው 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኖቹን ለንግድ በረራ መጠቀማቸውንና ደኅንነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ተከትሎ የወሰነው ውሳኔ እንደሆነም ገልጿል፡፡

እንዲሁም 36 አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ከ3 መቶ 30 ሺሕ በላይ ተጓዦችን ሲያጓጉዙ የደኅንነት ችግር እንዳልገጠማቸው አየር መንገዱ በዋቢነት ጠቅሷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የአየር መንገዱ አብራሪዎች፣ የበረራ መሃንዲሶች፣ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች እና የመስተንግዶ ባለሙያዎቹ በሙሉ ደኅንነቱ ለተረጋገጠ በረራ ዝግጁ በመሆናቸው የተወሰነ ውሳኔ መሆኑንም ማሳወቁን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!