የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ በድሬዳዋ ለማረፍ ሲቃረብ ችግር ገጥሞት እንደነበር አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ አውሮፕላኑ ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ ችግር ገጥሞት አንደነበር አስታወቀ።

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ የበረራ ቁጥሩ ኢቲ284 (ET248) የሆነው አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ መታየቱን ገልጿል።

ሆኖም አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉንና መንገደኞችን ያለምንም ችግር ማውረድ መቸሉን የጠቀሰው አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት እያጣራሁ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ችግር መንገደኞቹን ይቅርታ ይጠይቃል ብሏል።