ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ ኦ ኢ ኤም ሰርቪስ ከተሰኘው የአውሮፕላን አካላት አምራችና የጥገና አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ጋር የተደረገ ሲሆን፣ ለረጅም አመታት የሚቆይ መሆኑን የኩባንያው መረጃ ያመለክታል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው ለአየር መንገዱን ኤ350 ኤር ባስ አውሮፕላኖች መለዋወጫዎችን በማቅረብና የጥገና አገልግሎት በመስጠት ክትትል ያደርጋል፡፡
ይህም የአየር መንገዱን የአገልግሎት ውጤታማነት ለማስቀጠልና እያደገ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱ የኮቪድ-19 ተፅዕኖን በመቋቋም ውጤታማነት ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
የኦ ኢ ኤም ፕሬዚዳንት ዲዲዬር ግሬንጀር በበኩላቸው፣ የዓለማችን ስመ ጥር ተቋም ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መስራት በመቻላችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡