የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድነት ሽልማትን በድጋሚ አሸነፈ።
ሽልማቱን የሰጠው መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው እና በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አገልግሎት ጥራት፣ የሚሸልመው ስካይ ትራክስ የተሰኘው ተቋም መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ አየር መንገዶችም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀጠል የሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተከታታይ አራት ዓመታት የአንደኝነት ደረጃውን ጠብቆ ቆይቷል፡፡