የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ ስድስት ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው ወሰነ

ሚያዝያ 19/2013(ዋልታ) – የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ያካሄደውን ስብሰባ  ተከትሎ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

በዚህም ከስምንት ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ላለፉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የ6ሚሊዮን ብር ሽልማት እንዲሰጣቸው ውሳኔ ተላልፏል።

ሽልማቱም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያውን በሚያደርግበት ሐዋሳ ከተማ እንደሚሆን ተገልጿል።

በተጨማሪም ለክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከ17ዓመት በታች ውድድር ላይ ለሚሰሩት ስራ ድጋፍ የሚሆን የ3ሚሊየን 600 ሺህ ብር እንዲሰጥ እና ስራው በአግባቡ ስለመሰራቱ እያንዳንዱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክትትል እንዲያደርግ ተወስኗል።