ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ጉባኤ በዘጠኝ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅድስ አቡነ ማቲያስ ግምቦት 9/2014 ተጀምሮ ለ16 ቀናት የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ቤተክርስትያናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከረ መሆኑን ገልፀው በዘጠኝ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አስታውቀዋል።
ጉባኤው ያሳለፈው ውሳኔም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1. በ2014 ርክበ ካህናት ጉባኤ ቤተክርስቲያንዋ እና በሀገራችን ላይ ባጋጠመው የሰው ህይወት ህልፈት እና የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል ምልዓተ ጉባኤው በሰፊው ተነጋግሮ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጥሪ አቅርበዋል።
2. በስድስት ወራት ውስጥ የነበረው አፈፃፀም በመገምገም ያላለቁ ጉዳዮች አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ ፍፃሜ እንዲያገኙ መመሪያ ተሰጥቷል።
3. በሀገራችን ላይ ባጋጠሙ የሰላም እጦት ላይ በሰፊው ተወያይቶ ጦርነት እና የእርስ በእርስ ግጭት እንዲወገድ ቤተክርስቲያን የአስታራቂነት ሚናዋን እንድትወጣ ለፌደራል መንግሥት ጥያቄ እንዲቀርብ ተደርጓል።