የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 ተሸነፈ

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በናይጄሪያ አቻው 1 ለ 0 ተሸነፈ።

በህንድ ለሚዘጋጀው የ2022 የሴቶች ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ዙር ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግዷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠረበት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን በናይጀሪያ የሚያደርገ ሲሆን በድምር ውጤት የሚበልጥ ከሆነ ለዓለም ዋንጫው ማለፍ ይችላል።

በሚኪያስ ምትኩ