የኢትዮጵያ ኬንያ ወዳጆች ማኅበር ለኢትዮጵያ ያለውን አጋርነት ገለፀ

ኅዳር 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኬንያ ወዳጆች ማኅበር ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ኅልውና ለማፅናት የሚያደርጉትን ተጋድሎ እንደሚደግፍ አስታወቀ።

የማኅበሩ ሊቀመንበር እና የናይሮቢ የቀድሞ ከንቲባ ጆ አኪች በሚሲዮኑ አዲስ ለተመደቡ ዲፕሎማቶች እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ላይ ዛሬ ተገኝተው ባስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት በዚህ ፈታኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ልንቆም ይገባል ብለዋል።

የማኅበሩ አመራሮች የኢትዮጵያ እና ኬንያ ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በተለያዩ የኬንያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የትብብር መስኮች በተለይም የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩም መግለጻቸውን በናይሮቢ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።