የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ምስረታ ማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

ግንቦት 10/2014 (ዋልታ) ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና ኤፍኤስዲ አፍሪካ ገበያውን ለማቋቋም ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ገበያን ለመመስረት የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው ተብሏል፡፡

በስምምነቱ መሠረት አስፈላጊውን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ በኤፍኤስዲ አፍሪካ አማካኝነት የሚቀርብ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ምስረታው ሲጠናቀቅ፣ በአፍሪካ 30ኛው ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ይሆናል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም የኤፍኤስዲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ናፒየር ናቸው፡፡

በሰለሞን በየነ