የኢድ አልፈጥርና የሸዋል ኢድን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅተናል- የሀረር ከተማ ወጣቶች

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) የኢድ አልፈጥር እና የሸዋል ኢድ በዓላትን ለማክበር ወደ ክልሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን የሀረር ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።
የኢድ አልፈጥርና የሸዋል ኢድ በዓላት ስኬታማነት ለማክበር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል።
የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር እና በክልሉ በልዩ መልኩ የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓላትን በድምቀት ለማክበር እየተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንግዶቹ በሚመጡበት ወቅትም ተገቢውን አቀባበል ከማድረግ ባለፈ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ስፍራዎችን እንዲሁም ቅርሶችን ለማስጎብኘት መዘጋጀታቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመላክቷል።