የኢጋድ ዋና ጸሀፊ አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም 23/2014 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መረብ መንግስታት ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በነገው እለት ለሚከወነው በዓለ ሲመት አዲስ አበባ ገብተዋል::
ኢትዮጵያም በምርጫ ሂደት የመጀመሪያው የሆነውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የተከተለ የህዝብ ይሁንታን ያማከለ ምርጫን ማካሄዷ ይታወሳል::
ሰኔ 14 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫም ዜጎች ይበጀኛል ያስተዳድረኛል ያለውን መንግስት መምረጡን ተከትሎ በነገው እለት የመንግስት ምስረታ ይካሄዳል::
ይህን ተከትሎም በበዓለ ሲመቱ ላይ የሚታደሙ ዲፕሎማቶች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ይገኛል::
በሄብሮን ዋልታው