የኢፌዲሪ ባህር ሃይል የሰለጠነ ባለሙያ እያፈራ መሆኑ ተገለፀ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) የኢፌዲሪ ባህር ሃይል ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ተቋሙ የሚፈልገውን የሰለጠነ የባህር ኃይል ባለሙያ በማፍራት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የባህር ኃይል መሠረታዊ ባህርተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ም/አዛዥ ኮማንደር ከበደ ሚካኤል  ቢሾፍቱ ኢንጂነሪግ የሚገኙትን የባህር ኃይል አባላት በውሃ ዋና የሚሠጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል ስልጠና ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፤ የሃገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችልና ከውጭና ከውስጥ የሚመጡ ችግሮችን የሚጠብቅ ዘመናዊ የሆነ ባህር ሃይል ሠራዊት ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ ነው ፡፡

ሠልጣኝ አባላትም እንደተናገሩት ተልዕኮዎችን የሚወጣ ጠንካራ የሆነ ባህር ሃይል አባል መሆናችንን አውቀን የሚሠጠንን የውሃ ላይ ግዳጅ ሥልጠና በብቃት እንወጣለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡